የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ከማእከል እስከ ወረዳ ድረስ ካሉት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ለሃገራዊ ጥሪ ተግባራዊ ምላሽ ዙሪያ በተካሂደ ውይይት እንዳሉት ድል ካለመስዋዕትነት አይገኝም! የጁንታው ቡድን ኢትዮጵያን የማፍረስ የህልውና አደጋ ቃትቶብናል፤ እንደ አንድ ልብ መካሪ፤ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን በመትመም የተቃጣብንን አደጋ ቀልብሰን ድል እናድርግ ብለዋል፡፡
“በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ሀገረ-ትግራይን እንመሰርታለን” የሚል የቀን ቅዠትን ይዘው ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ላይ ይገኛሉ፤የጁንታዉ ዋነኛ አጋር የሆኑት ኦነግ ሸኔና ቅጥረኛ የእናት ጡት ነካሾች የተቀናጀ ጥፋት እየፈፀሙ ይገኛሉ ብለዋል ።
በመሆኑም ኢትዮጵያን ከማፍረስ ሰይጣናዊ ሕልማቸው ጋር አብሮ ለመቅበር ከመቼውም በላይ በአንድነት፣ በፅናት ከጀግናዉ የመከላከያ እና የፀጥታ ሀይሎቻችን ጎን እስከ ህይወት መሰዋትነት መክፈል ድረስ ልንሰለፍ ይገባል።
መላው የከተማችን አመራር፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ነዋሪዎች እየተካሄደ ያለዉን የህልውና ጦርነት ዉስብስብ ባህሪ ተገንዝበው ሙሉ ትኩረታቸውንና አቅማቸው ኢትዮጵያን ማዳንና የከተማችንን ሰላም ማስጠበቅ ላይ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ሰሞኑን በአዲስ አበባም የጁንታውን አረመኔያዊ ተግባር በመደገፍ የተለያዩ እንቅስቃሴ ባካሄዱት ላይ የጀመርነውን በከሃዲዎች ላይ የህግ የበላይነትን የማረጋጋጥ ስራችንን አጠናክረን ቀጥለናል ሲሉ ተናግረዋል።