በማስጀመርያ መርሀግብሩ ላይ ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ ቃል ተገብቷል።
የገበታ ለሀገር ምዕራፍ ሁለት የሀብት ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እስካሁን ተደራሽ ያልሆኑ ታላላቅ ሐገራዊ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል ነው ፡፡
የገበታ ለሐገር ምዕራፍ ሁለት የሐብት ማሰባሰቢያ የሀገር ውስጥ የባለሀብቶች አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመክፈቻ መርሐ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “ሰሞኑን ሀገራችን የከረመችበትን ውጥረት አልፈን ዛሬ ለልማት አሻራችንን ልናስቀምጥ መገናኘታችኝ ፈጣሪ ይመስገን ብለዋል።
ተስፋ ቆርጠን አናውቅም ይልቁንም በጋራ በመስራት እና በመትጋት የጀመርናቸውን ፕሮጀክቶን ጨርሰን-አሻራችን ለሚቀጥለው ትውልድ እናስቀምጣለን ሲሉ ገልፀዋል።
ሪቫን በመቁረጥ ተስፋ ሊያስቆርጡን የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በጋራ እናልፈዋለን እንጂ ምንም ጊዜም ተስፋ አንቆርጥም ያሉት ከንቲባዋ ገበታ ለሐገር የተባበረ እጃችን የሚገነባው ፕሮጀክት ነው” ብለዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተለያዩ የግል ባለሐብቶች የመንግስት የስራ ሓላፊዎች ተገኝተውበታል፡፡
በዚህ ምሽት ከራስ በላይ ለትውልድ ለታሪክ አሻራ ለማሳረፍ 1 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ 1.2 ቢሊየን ብር ቃል ተገብቷል።