የባለፈው ወር መጨረሻ አካባቢ የግንባታ ውል ከተደረገባቸው ፕሮጀክቶች መካከል የሆነው የግብርና ምርት ገበያ ፕሮጀክት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ላይ የግንባታ ስራ ተጀምሯል።
የፕሮጀክት ስራውን የሚያከናወነው የኦቪድ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በተቀመጠው የግዜ ቀነ ገደብ ለማጠናቀቅ የግንባታ ቦታውን ምቹ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ፡፡
የግብርና ምርት ገበያ ግንባታዎቹ ሲጠናቀቁ በአዲስ አበባ የገበያ ተደራሽነትን በማስፋት፤ አምራችና ተጠቃሚን ማገናኘትና የዋጋ ንረትን መከላከል ላይ ጉልህ አበርክቶ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡