የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ሆስፒታሎችን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አመስግነዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው የወደሙ ሆስፒታሎች በመልሶ ማቋቋም እየደገፉ ለሚገኙ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ሆስፒታሎችን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አመስግነዋል፡፡
እስካሁን በተደረገ ርብርብ አብዛኞቹ ሆስፒታሎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩና ቀሪዎቹም በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል፡፡
ቀሪ ተቋማትም በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሥራ የሚገቡበት አሰራር ከወረራ ነፃ እንደሆኑ የሚተገበር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ተቋማቱ ከወረራ በፊት ወደነበሩበት ቁመና የመመለሱ ሥራ የመንግስትን አቅም፣ ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን እንዲሁም የዳያስፖራ ማኅበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ በቀጣይ ወራቶች የሚተገበር እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡