‹‹ህዝባችን ልብ እንዲለው የምንፈልገው ጉዳይ ምንም የፖለቲካ ሃሳብ የሌላቸው ፤ ሃሳባቸውን አቅርበው ህዝብ አወያይተው ፤ እንዲመርጣቸው ማድረግ ያልቻሉ፤ ዛሬ የህዝባችንን እሴቶች በመሸርሸር ላይ ይገኛሉ።
የህዝብ አብሮነትና አንድነት ፤ ወደ ኋላ መልሶ በመከፋፈል በተራ ስድብ እሴቶቻችንን በመሸርሸር ፤ ወጣቶችን ስራ ከማስያዝና ነጋቸውን በመገንባት ፋንታ የወረደ ስብእና እንዲላበሱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ የጀመርነውን ከህዝብ ጋር አብሮ የመስራት ሁኔታ ለመሸርሸር ይሰራሉ፡፡
ይህ በመንግስት ብቻ ሳይሆን ህዝቡ ራሱ እምቢ ማለት አለበት፡፡ አብሮነታችን ከዚህ በላይ ማደግ አለበት ፤ትውልዱ የላቀ ስብእና መላበስ አለበት ፤የፖለቲካ ልዩነት በመድረክና በሰለጠነ መንገድ በመድረክ ብቻ ነው መስተናገድ ያለበት፡፡
መንግስትንም መተቸት ይቻላል ፤ግን በሰለጠነ መንገድ ፤ በሁከትም አይደለም ፤በስድብም አይደለም፤ እርስ በእርስ በማዋረድም አይደለም፡፡ የመረጠ ህዝብ ድምፁ መከበር አለበት፡፡ ››
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ