የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጋር በመሆን የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ሂደትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፤ተፈታኝ ተማሪዎችን በማበረታታት መልካም ዕድልን ተመኝተዋል።
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 62 የፈተና ጣቢያዎች ለ36 ሺህ 401 ተማሪዎች እየተሰጠ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው በመላ ሀገሪቱ 617,000 ተማሪዎች ለመፈተን መመዝገባቸውንና ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል 91.5 በመቶ የሚሆኑት በዛሬው ዕለት ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡