በዛሬው ዕለት የተጀመረው 12ኛ ክፍል ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዕለት ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዕለቱ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት እና በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፈተና ሳይፈተኑ ከወጡ ተማሪዎች ሪፖርት ውጪ አጠቃላይ ሂደቱ በመላ ሀገሪቱ ፈተና ከሚሰጥባቸው 130 የፈተና ጣቢያዎች በ128ቱ ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ የተሳካ እንደነበር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።
ከዩኒቨርሲቲዎቹ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፈተና በተሰጠባቸው ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናው በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን ተማሪዎች በነገው ዕለት ለሚኖራቸው ፈተና ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለደረሰው ጉዳት ልባዊ ኀዘኑን ገልጿል።