1479ኛው የመውሊድ በዓል በታላቁ የአንዋር መስጅድ በድምቀት ተከብሯል ። ።
የነብዩ ሙሀመድ መወለድን ተከትሎ የሚከበረው መውሊድ ነብዩ መሀመድ ለሰው ልጆች ያስተማሯቸው እና በድርጊትም ያሳዩትን የእዝነት፣ የይቅር ባይነትና የመረዳዳትና ሌሎች ተምሳሌትነት የሚወደሱበት ለተቸገሩት እርዳታ የሚለገስበት መሆኑ ይገለፃል።
የመውሊድ በዓል የነብዩ ሙሀመድ አስተምህሮዎች የሚወሳበት እና የሚወደሱበት እንደመሆኑ መጠን ህዝበ ሙስሊሙ የነብዩ ሙሀመድን አስተምህሮ በመተግበር እንዲያከብር ያነጋገርናቸው የእምነቱ አባቶች ገልጸዋል።
በበዓሉ ላይ የታላቁ አንዋር መስጅድ ኢማም ሸህ ጣሃ መሀመድ ሀሩንን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ጉባኤ ፀሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ምዕመኑ በታላቁ አንዋር መስጅድ ተገኝተዋል።