እንደ ሀገር ከ28 ዓመታት በኋላ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የተሰጠው የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት 73 ሺህ 667 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም 80.2% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዚያ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣይ ክፍል ሲያልፉ ፤ 67 ሺህ 939 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 56 ሺህ 842 የሚሆኑት 83.6% የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።
የትምህርት ግብዓት ለማሟላት እያደረግን ያለው ጥረት እና መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ተማሪዎችን ብቁ የማድረግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት የሰሩት ስራ ተማሪዎቹ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በማስቻሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
ሃገሩን የሚወድ ጠንካራ ትውልድ ለመገንባት ና የትምህርት ጥራትን የማስጠበቅ የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ