የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት እና የግል አጋርነት መርሀ ግብር የ60ሺህ መኖርያ ቤቶች ቅድመ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተካሄዷል::
ቤቶቹ በ5 አመታት ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የሚጠናቀቁ ሲሆን ከ250ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከተማች ወጣቶች ቀጥተኛ የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ይሆናል::
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመኖሪያ ቤት የህዝቡ ቀዳሚ ጥያቄ በመሆኑ በመንግስትና በግል ተቋማት ትብብር መስራት የሚያስችል የፖሊሲ እቅጣጫ እና የአሰራር መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል::
በመኖሪያ ቤት ግንባታ ለመሰማራት ፍላጎት ካሳዩ 70 የግል ድርጅቶች ውስጥ ኦቪድ ግሩፕ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ በቅድመ ማስጀመሪያ ስነ-ስርአት በመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ዙሪያ እና ባከናወናቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ለአስተዳደሩና ለባለድርሻ አካላት ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን 60ሺህ ቤቶችን በ5 አመታት ውስጥ ገንብቶ ለተጠቃሚዎች የሚያስተላልፍ ይሆናል::