የጋራ መኖርያ ቤቶችን ግንባታ በተያዘላቸው ግዜ ያለማጠናቀቅ ክፍተት መኖሩን የገመገሙት ከንቲባ አዳነች ለዚህ ችግር የሲሚንቶ እጥረት፣ የተለያዩ የግንምባታ ግብዓቶች ዋጋ መጨመር እና ዋጋ ልዩነት ፤ የባንክ ብድር እጥረት ፣ የተቋማት በቅንጅት አለመስራት እንዲሁም የወሰን ማስከበር ችግር መኖሩን ተገንዝበናል ብለዋል።
ሆኖም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ፣ የጋራ መኖርያ ቤቶችን መሰረታዊ ግንባታ መንግስት በአፋጣኝ በማጠናቀቅ፣ ቀሪውን ተጠቃሚው እንዲያሟላ የሚደረግ ሲሆን የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ቀሪ ስራዎችን በቅንጅትና በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ይህንንም የሚከታተሉ ተቋማትና ኮሚቴዎች በየሳምንቱ የግንባታውን ሂደት ይከታተላሉ ብለዋል።
በምክኒያትነት የተነሱት የግብዓት እጥረትና የዋጋ ልዩነቶችም አፋጣኝ እልባት አግኝተው እስከ ሰኔ ወር ባለው ግዜ ግንባታዎቹ ተጠናቅቀው ለተጠቃሚው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።