‹‹በፈተናዎች ውስጥ ሆነን ያከናወናቸው ተግበራት ብዙ ትርጉም አላቸው፤ ምንም ውዥንብር ቢኖር ፤ምንም አይነት ተግዳሮት እና ፈተና ቢኖር ሊያስቆመን እንደማይችል፤ ጠንካራ ህዝቦች መሆናችንን፤ በፍፁም ተስፋ እንደማንቆርጥ ፤በየትኛውም ፈተና ውስጥ ሆኖ የሚያስፈልገው መስራት መደማመጥ ፤መተማመን እንደሆነ አይተናል፡፡
ስራዎቹ ኢትዮጵያ በድል እየቀጠለች እንደሆነ ማሳያ ናቸው፡፡
ብዙ የሚቀሩን ስራዎች እንዳሉም እናውቃለን፤ ለዚህ የሚያስፈልገን መተባበር ፤የሚያስፈልገን መደማመጥ ፤የሚያስፈልገን ስንፍናን ማስወገድና መስራት ነው፡፡ የሚሰራን መደገፍ ነው፡፡ ለሚሰራ ጉልበት ሞራል ሆኖ ማሰራት ነው፡፡ሌብነትን መታገል ነው፡፡ውስን ሃብታችን ከድሆች አፍ እንዳይነጠቅ መከላከል ነው፡፡
ጀመርን እንጂ ገና ብዙ እንሰራለን፤መስራትም እንችላለን፤ ለመስራትም ደግሞ ሁልጊዜ ህዝባችንን ይዘን እንተጋለን!!››
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከተናገሩት