ጀግንነት ጀግንነት ቀንን በማስመልከት መልዕከት ያስተላለለፉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ኢትዮጵያ እና ጀግንነት የሚነጣጠሉ አይደሉም በዚህ ወቅትም ለኢትዮጵያ ሰላምና ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚዋደቁ ብዙ ጀግኖችን አፍርታለች ብለዋል።
ኢትዮጵያዊ ሆነን ደካማነትን ከሀዲነትን እና ባንዳነትን ልናወርስ አንችልም ልንወርስም አንችልም፡፡ ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ጀግና ማፍራት ማይታክታት ኢትዮጵያ ከዘመን ዘመን ከትውልድ ትውልድ ክብሯን የጠበቁ ስምዋን ያስጠሩ አጥታ አታውቅም፡፡ ክብራቸው ተገፎ ሜዳ ላይ የተበተኑት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊትም የኢትዮጵያ ጀግኖች መሆናቸውን እናውጃለን ብለዋል፡፡
”በአሁን ሰዓትም እናት ሀገራቸውን ከባንዳ ለመጠበቅ ህይወታቸውን ጨምሮ የሚችሉትን ሁሉ እየሰጡ የኢትዮጵያን ሰላም ፤ ሉአላዊነት እና የህዝብዋን ደኅንነት ለማከበር እየተዋደቁ ሀገርን ከመበተን ያዳኑ የሰራዊትት አባላት እና መላው የጸጥታ ሀይል ጀግኖች በመሆናቸው ስናደንቃቸው ስናከብራቸውእና ስንዘክራቸው እንኖራለን፡፡” ብለዋል፡፡
ጀግንነት ማለት ራስ መውደድን ንቆ ሌሎችን የበለጠ መውደድ ከራስ በላይ ለሌሎች መሆን ነው ያሉት ም/ከንቲባዋ ኢትዮጵያዊ ጀግንነት በጦር ሜዳ ብቻ በመፋለም የሚገለጽም አደለም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን ሆና እንድትቀጥል አቅማቸው በፈቀደ ሁሉ እያደረጉ ያሉ ሁሉ ጀግኖች ናቸው ብለዋል፡፡
”ባለፉት 2 አመታት አለምን ያሸበረውን የኮሮና ቫይረስን አደጋ ለመከላከል በርካታ ጀግኖች ከጦር ሜዳ በማይተናነስ ሁኔታ የህክምና ሞያቸውን ከፍ አድርገው ለህዝባቸው ሲሉ ቤታቸውን ጥለው ዘምተዋል ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ እነሱም ጀግኖቻችን ናቸው እናመሰግናለን ብለዋል፡፡“
በተሰማራንበት መስክ ሁሉ ሀገራችንን በታማኝነት እና በሀላፊነት ስሜት ማገልገል ጀግንነት ነው ያሉት ም/ከንቲባዋ የሀገራችንን ስም የከተማችን ሁኔታ ለማተካከል እና የህዝብን ህይወት ለመቀየር በወጣንበት በወረድንበት መንገድ ሁሉ ጥርጊያዉን ሲያሳምሩ ራሳቸውን ከሌብነት እና ከሙስና ነጥለው ህዝብን በማገልገል የሚተጉ ከታየው መሰናክል ይልቅ የኢትዮጵያ ተስፋ እና ብሩህ ቀን የሚታያቸው ለትንሳኤዋ የሚተጉ እነሱም ጀግኖቻችን ናቸው ብለዋል፡፡
በዚህ ወቅት ሁሉም ሰው የአገሩ አርበኛ ነው፡፡ ሀገርን በቅንነት ማገልገል ጊዜ ጉልበትን ለሀገር ጥቅም ማዋል ትልቅ ጀግንነት ነው ያሉት ም/ከንቲባዋ ሊተመን የማይችል ህይወታቸውን እየሰጡ ያሉ ጸጥታ ሀይሎቻችን ግን ከጀግኖች ሁሉ የላቁ ጀግኖች ናቸው ብለዋል፡፡
የህይወት ዋጋ ከፍለው በነጻነት በክብር በሰላም እንድንኖር ያደረጉንን ጀግኖች በሙሉ ቅድሚያ በመስጠት ልናገለግላቸው ልዩ ክብር ልንሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡
“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክ/ከተማ በሁሉም አካባቢ በሚሰጠው አገልግሎት ሁሉ ለጀግኖቻችን ቅድሚያ በመስጠት ለማገልገል መወሰኑን እገልጻለው“ ብለዋል፡፡
“በበረሀ በህዳሴ ግድብ ግንባታም ይሁን በሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሌት ተቀን እየሰሩ ያሉ እንዲሁም በአለም አደባባይ የሚሟገቱ ትላልቅ ጀግኖች ናቸውና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡“ ብለዋል፡፡