ይሄን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ 8 የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማልማት የ‘ገበታ ለትውልድ’ ሐሳባችንን ገፍተንበታል። የዐርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርትን በ120 ሄክታር መሬት ላይ፣ የአባያ ሐይቅን እያየ በሚያማምር ቦታ ላይ እንዲገነባ ዛሬ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠናል።
በዓመት ከመንፈቅ ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቀው ይህ ፕሮጄክት 1.3 ትሪሊዮን ዶላር የሚሸፍነውን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢን ተቋዳሽ እንድንሆን ያደርገናል። ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሀብታችንን በመጠቀም ሀብት የማፍራት ጅምሮችን በማስፋፋት፣ የብልጽግና ጉዟችንን ለማሳካት እንተጋለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ