ለውጥ በተግባርና በተጨባጭ !!
ጎስቋላና ለመኖር ፈፅሞ ተስማሚ ባለሆነ አካባቢ የተተገበረው የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የነረውን ገፅታ በዚህ መልኩ ቀይሮታል፡፡
ዛሬ ለምረቃ የበቃው፡-
• ከ3 ሺህ በላይ ዜጎችን መመገብ የሚችለውን እንደ ከተማ 7ኛውንና ትልቁን የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከል
• ከበቦታው የነበሩ ጎስቋላ ቤቶችን መልሶ በመገንባት 8 ዘመናዊ የመኖርያ ቤቶችን ፤
• እንዲሁም በአካባቢው እጅግ አስቸጋሪ በሆነ የሸራ ሱቆች የንግድ ስራ ሲሰሩ የነበሩትን የንግድ ቤቶች ዘመናዊ በሆኑ 28 የንግድ ሱቆች በመቀየር ፤
• የሸገር ዳቦና የአትክልት መሸጫ ሱቅ
• እነዚህ ፕሮጀክቶች ከአካባቢው ሞዴል የአረንጓዴ ልማትና የከተማ ግብርና እንቅስቃሴ ጋር እንዲያያዝ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ የምገባ ማእከሉ የአትክልት ምርቶችን እዛው እንዲያገኝ ለማድረግ የታሰበም ጭምር ነው፡፡
• የምገባ ማዕከሉ ለ60 እናቶችና ለ12 የጥበቃ ሰራተኞች ቋሚ የስራ እድልን የሚፈጥር ነው፡፡