በ2015 በጀት ዓመት 100 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደን 107 ቢሊዮን ብር በመሰብስበን በርካታ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ገንብተናል፡፡በ2016 በጀት ዓመት 140.29 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደናል ፤ ይሄንን እቅድ ለማሳካት ግብር ከፋዮቻችንን ማበረታታት ተገቢ ነው።
በመሆኑም ዛሬ የ2016 በጀት ዓመት ገቢ የማሰባሰብ ንቅናቄን አስጀምረናል።
የሰበሰብነውን ገንዘብ መልሰን ለዘላቂ ልማት፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ፣ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር እንዲሁም የንግድ እንቅስቃሴውን በማነቃቃት የላቀ ሚና ለሚጫወቱ ፕሮጀክቶች በማዋልና የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል በታማኝነት እንሰራለን።
ከችግሮቻችን እና ፈተናዎቻችን በላይ ከፍ ብለን በመፍጠንና በመፍጠር በትጋት መስራታችንን እንቀጥል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ