ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ጋር በመተባበበር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የውል ስምምነት የተፈራረመው ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ምዝገባ በተጠናቀቀባቸው የተለያዩ ሳይቶች ከ1ሺህ በላይ ቤቶችን ለመገንባት ማህበር መመስረቱን አስታወቀ፡፡
ምዝገባ ተጠናቆባቸው ማህበር ከተመሰረተባቸው ሳይቶች መካከል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቡልጋሪያ እና የላንቻ ቤት ማህበራት በጠቅላላ ጉባኤ በመወሰን ከቂርቆስ ህብረት ስራ ማህበር ጽህፈት ቤት ጋር ጉባኤውን አካሂደዋል፡፡
በተጨማሪም በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኘው እና ምዝገባው የተጠናቀቀው የጣሊያን ኤንባሲ ሳይት እና በመጠናቀቅ ላይ ያለው የጎሮ ሳይት ተመዘጋቢዎችንም በቅርቡ በማህበር በማደራጀት ወደ ግንባታ የሚገባ መሆኑንም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ገልፆል፡፡
በማህበራቱ ባደረጉት ጠቅላላ ጉባኤም የቤት ግንቢውን አካል የፋይናንስ ፣ የኦዲት ፣ የግንባታ እና የጥራት ቁጥጥር ስራ የሚያከናውኑኮሚቴዎችን መርጠዋል፡፡