ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አልጋ ወራሽ ሼክ ሞሃመድ ቢንዛይድ አልናህያን እንዲሁም ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ህዝብ የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እገልጻለሁ ብለዋል።