የአፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጅግጅጋ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጂግጂጋ ሲደርሱም የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሶማሌ ክልል ቆይታቸውም በክልሉ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ230 ሺህ በላይ እንስሳት ሲሞቱ፥ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ከክልሉ ያገኘነው መረጃያመላክታል፡፡
FBC