ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74(2) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የሚከተሉትን ሹመቶች እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፦
1. ዶ/ር አለሙ ስሜ – የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
2. ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ – የማዕድን ሚኒስትር
3. ዶ/ር ግርማ አመንቴ – የግብርና ሚኒስትር
በተጨማሪም ከጥር 10፣ 2015 ጀምሮ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰተዋል፦
1. አቶ ማሞ ምሕረቱ – የብሔራዊ ባንክ ገዢ
2. ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
3. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት – የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር
4. አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ – የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር
5. አቶ መለሰ አለሙ – በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት
ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ