የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ገቡ።
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና ከፍተኛ መንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ ከዚህ ቀደም በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ፕሮጀክት ግንባታው የተጀመረውን የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት እንደሚጎበኙ ይጠቃል ሲል የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼