ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአማራ ክልል መስተዳድር በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ባዘጋጀው የምስጋና እና የዕውቅና መርሐ ግብር ላይ ለፌደራል የጸጥታ አካላትና ተቋማት ሽልማት አበርክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድነት ለጋራ ዓላማ መቆም ተግዳሮቶችን ለመሻገር እንዲሁም ለሀገር ዘላቂ ብልጽግናን ለመገንባት አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።