ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2023 የፈረንጆች አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፥ “ለመላው ወዳጆቻችን እና አጋሮቻችን መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላቸው እመኛለሁ” ብለዋል።
አዲሱ ዓመት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘላቂ ሰላም እና ደህንነትን ይዞ እንዲመጣም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።