የፊታችን ጥቅምት 24 ሁለተኛው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሽብር ቡድኑ ህወሀት የደረሰበትን ግፍ መታሰቢያ እንደሚካሄድ የመንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
የመንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደዔታ ከበደ ደሲሳ በሰሞነኛ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
ጥቅምት 24 /2013 ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሽብር ቡድኑ ህወሀት የተፈፀመበትን ጥቃት በሀገር እና በወገን የተፈፀመ ክህደት ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል ብለዋል።
ዕለቱ አሁንም ድረስ ለዘለቀው እና መንግስትና ህዝብ ተገዶ ለገባበት የሀገርን ህልውና የማፅናት ትግል ሰበብ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ደዔታው ዕለቱ ኢትዮጵያዊያን ሁሌም እንዲያስታውሱት ይደረጋልም ብለዋል።
የፊታችን ጠቅምት 24 ለሁለተኛ ጊዜ “ጥቅምት 24 መቼም አልረሳም “በሚል መሪ ቃል ታስቦ ይውላል ብለዋል ሚኒስትር ደዔታው።
በመላ ሀገሪቱ በሁሉም የመንግስትና የግል ተቋማት ታስቦ በሚውለው ዕለትም የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሽብር ቡድኑ ስለደረሰበት ግፍ እየከፈለ ስላለው ዋጋ የሚያስቡ መርሀ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል።
በዕለቱ ማለዳ 4 ሰዓት ለአንድ ደቂቃ ያክል ተማሪዎች፣ አሽከርካሪዎችንና የፀጥታ ሀይል አባላትን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቆሞ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን አጋርነት ያሳያልም ተብሏል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ተጋድሎ ለማሰብ በተዘጋጁ መርሀግብሮችም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በንቃት እንዲሳተፍም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደዔታው አቶ ከበደ ደሲሳ ጥሪ አቅርበዋል።
ፍቅሩ ነኝ, Toosh Tarree Page and 384 others
67 Comments
116 Shares
Like
Comment
Share