በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በሰላም ስምምነቱ እልባት እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የማመስገንና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ በመካሄድ ላይ ነው።
በመረሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።