በእለቱ በማለዳ በሁሉም ክፍለከተሞች አካባቢን ማጽዳት፤ ችግኝ ተከላና የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎችን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃለፊዎችም ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ተገኝተው የበጎ ፍቃድ ቀንን አካባቢን በማጽዳት አስጀምረዋል፡፡
“ዛሬ አመቱን ሙሉ በበጎነት ስናከናውን የቆየነውን ተግባር የምናጠናቅቅበት ዕለት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዕለቱ ከሁሉም በላይ አሸባሪውን ህወሃት በከፈተብን ጦርነት ለኛ መኖር፤ ለኛ ሰላም እና ለሉአላዊነት ሕይወትቱ በመስጠት መስዕት እየከፈለ ያለውን ለመከላከያ ሰራዊታችን እንዲሁም ጥምር ጦሩ እየሰጡ ያለውን ጎነት የለምና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ከጳጉሜ እስከ ጳጉሜ በጐ ፍቃደኞችን በማሰተባበር የተለያዩ የሠብዓዊ ተግባራትን አከናውናለች።
ቤቶች ግንባታና እድሳት
በበጎ ፍቃድ ተግባራት በከተማ አስተደደሩ በዓመቱ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 37,015 አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ያደረጉ 8,000 አዳዲስ ቤቶች ግንባታና እድሳት ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን በነበሩት ጊዜያት ውስጥ ተከናውነዋል።
ዳቦ ማምረቻ ፋብርካ
ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ዳቦ ፋብሪካ ግንባታና መሸጫዎች መሻሻያ በደምሩ 106 ግንባታዎችተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል::
ምገባ ማዕከላት ግንባታ
ዘንድሮ የተገነቡትን ጨምሮ 13 የምገባ ማእከላት ተገንብተው ከ30 ሺሀ በላይ የእለት ጉርስ ማግኘት የማይችሉ የከተማዋ ነዋሪዎች መመገብ ተችሏል።
በማህበረሰብ ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎች በድምሩ ከ4.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ተግባራት ተከናውነዋል።
አሮጌ ሊባል ቀናት በቀሩት 2014 ዓ.ም በሰው ተኮር ስራዎች ህዝቡንና ባለሀብቱን በማስተባበር ውጤታማ ስራ መስራት ተችሏል። የከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰቡን በማስተባበር በጎ ፍቃደኝነትን ባህል ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶት እየተሰራ ነው።
የበጎ ፈቃድ ስራች የህብረተሰብን አኗኗርን ሊያሻሽሉና ሊለውጡ እንዲሁም ሃገርን ሊያሳድጉ የሚችሉ ተግባራት በመሆናቸው የየራሳችንን አሻራ በማሳረፍ የከተማችን ብሎም የሃገራችን እድገት ማፋጠን ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል፡፡