ጳጉሜን 1 የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ(ዶ/ር) እና የጠ/ሚ ፅ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር አለምፀሃይ ጳውሎስ በጋራ በመሆን የሃገር አቋራጭ አውቶቢስ አሽከርካሪዎችን እና በዘርፉ ላይ ያሉ አካላትን ስለአገልግሎታቸው አመስግነዋል::
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ያሉ አካላት ስለአገልግሎታቸው ምስጋና ይገባቸዋል ያሉ ሲሆን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ በማሽከርከር ወገኖቻቸውን እንዲያገለግሉ አደራ ብለው ቃለ መሃላም አስፈፅመዋል::