ጳጉሜ 3
የሰላም ቀን!!
የሰላም ዋጋዋ ውድ ነው፡፡ ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት ነው፡፡ ሰላም አገር እንዲኖረን፤ሰላም ሰርተን እንድንኖር ፤ ሰላም ወልዶ ለማሳደግ፤ ሰላም የሰው ልጅ ህልውናው እንዲረጋገጥ ፤ በእርጋታ ማህበራዊ ህይወቱን እንዲመራ ሰላም በእጅጉ ወሳኝ ነገር ነው፡፡
ከብዙ ውድ ነገሮቻችን ሁሉ የሚበልጠው ሰላም ነው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ለሰላም ያለው አቋም ዘላቂና የማይናወጥ ነው። ከእራሱ አልፎ ለአህጉሩ፤ ከአህጉሩም አልፎ ለዓለም ሰላም አንዲሆን በርካታ ስራ የሰራን እንደሆንንም በአህጉራዊ እና በዓለምዓቀፍ መድረክ ላይ በእውቅና እና በምስጋና የተመሰከረልን ህዝብ እና ሀገር ነን። ሰላም ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ተግባር በመሆኑ ሀገራችን ለራስዋ ሰላምና ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት ሰላም ግንባር ቀደም ሚናዋን እየተወጣች እንደሆነች ይታወቃል ለባለፉት አመታት የሃገራችንን እና የህዝባችንን ሰላም ለማደፍረስ በርካታ እኩይ ጥቃቶች ደርሰውብናል።
የከተማችን ነዋሪ ሰላም ወዳድ ህዝብ ነው፤ የራሱንና አካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ብዙ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፤ አሁንም ይህነኑ እያደረገ ነው፡፡
ይህም ሲሆን ለህግ ክብር እና ለፍትህ ብለን ጥቃቱን በድል ስትመልስ ቆይታ፤ ሁሌም የሚያዋጣው የሰላም መንገድ እንደሆነ አምና ስራዋን ቀጥላለች። የከተማችንን ሰላም የማስጠበቅ ሀላፊነት የሁሉም ማህበረሰብ መሆኑን በማስገንዘብ ከህዝቡ የተወጣጡ የሰላም ሰራዊት ግንባታ በማደራጀት ከተማችን በሁሉም ረገድ ሰላምዋ የተጠበቀ እንዲሆን ተግተን እንስራ!!
የከተማችን ሰላም የምናስጠብቀው እኛው እራሳችን ነን፡፡የሀገራችን ሰላም ለሁለንተናዊ እድገታችን ምሰሶ ነው፡፡ ለዘላቂ ሰላማችን በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ያለውን የኢትዮጵያ የሰላም አምድ የሆነውን መከላከያችን ጎን ሆነን እኔ የሰለም ዘብ ነኝ ብለን ለሰላማችን እንቁም፡