ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የተጀመረውን የአለምና አህጉር አቀፍ ዩንቨርሲቲዎች ስፖርት ፌደሬሽን ፎረም እንዳሉት የ2063 አፍሪካዉያን በጋራ የመበልጸግ አጀንዳ እውን የሚሆነው የአባል ሀገራትን ፍላጎት ተጠቃሚነትና መተሳሰብን ሲረጋገጥ ነው ብለዋል ፡፡

ፓን አፍሪካኒዝም ልዩ የሚያደርገው በአፍሪካውያን ማንነት ኢኮኖሚና ባህል ውስጥ ትልቁን ስፍራ የሚሰጠው የማንነት መገለጫዎች ውስጥ ደግሞ ስፖርት አንደኛው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ታሪክ እንደሚነግረን በአፍሪካ የመጀመሪያዋ የሊግ ኦፍ ኔሸን አባል አገር የሆነችው ኢትዮጵያ ወራሪ የቅኝ ገዢዎች ላይ ድል በመቀዳጀት ለቀሩት የአፍሪካ ሀገራት የነጻነት ተምሳሌት በመሆን ቀዳሚ ሀገር ናት ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ ፡፡ አፍሪካዊያን በ2063 ሁሉን ያማከለና አሳታፊ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማሳካት ያቀዱትን ራእይ ለማሳካትና ወደ ፓን አፍሪካኒዝም የሚያደረጉትን ሽግግር እውን ለማድረግ በአንድነት በጋራ በመቆም ለጋራ ብልጽና ሊሰሩ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡