የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) የአዲስአበባ ቅርንጫፍ የ2013 ዓ.ም ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ተካሄደ
“አንድነት ለልማት” ኦ.ል.ማ በዘንድሮ የስራ አመት በከተማችን ባሉ ክ/ከተሞች ካፈራቸው 55 ሺህ በላይ አባላት ያሰባሰበውን ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ አዲስ አበባን ሊያለማበት ወስኖ የልማት ግባዓት እንዲሆነው የጠየቀንን መሬት አስረክበናል። ይህንን የልማት ቦታ ስንሰጥ በተባለው ልክ እና በተባለው ጥራት እንደሚሰራ እምነቱ አለንና ይህንን ለከተማችን እድገት እና ውበት ለመስራት ከቆረጠው ኦ.ል.ማ ጎን በመቆም በአንድነት ልማታችንን እና ብልጽግናችንን እናረጋግጥ ለማለት እወዳለሁ። ፕሮግራሙ ላይ በድንገት የተገኛችሁና ያደመቃችሁን መሪዎቻችንን እና እንግዶቻችንን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።