ፓርኩን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ከመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታአቶ ጌታቸዉ ኃይለማርያም ፣የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ባለድርሻ አካላትና የአካባቢዉ ነዋሪዎች በተገኙበት ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የማዕከሉ በዚህ ደረጃ ከፍ ባለ የስነ ምህዳር እና የመካነ እንሰሳት ማዕከልነት ደረጃ መገንባቱ ከተማችንን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ይዘን የተነሳው አንዱ ዉጥን ማሳያ ጅማሮ ነዉ ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ለማዕከሉ የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በማዕከሉ ግንባታ ወቅት ተሳታፊ ለነበሩ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በ ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ፤ጭላዳ ዝንጀሮ፣ ሚዳቋና ሌሎች ከ12 በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ከ53 በላይ እንሰሳት በፓርኩ ይገኛሉ።የፒኮክ መናፈሻ አዲስ ዙ ፓርክ የመከላከያ ሚኒስትር የኮንስትራክሽን አማካኝነት የተገነባ ነው።