ከጥር 26-28/ 2015 ዓ.ም የሚቆይ 14ኛው ከተማ ዓቀፍ የባህል ፌስቲቫል “ባህሎቻችን የአንድነታችን ካሰማ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ፌስቲቫል ነው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባህል የአንድ ማህበረሰብ ማንነት የሚቀዳበት ፥ አንድን ማህበረሰብ ከሌላው ማህበረሰብ ትስስር የሚፈጥርበት ጠንካራ ገመድ ነው ብለዋል።
የአንድ ማህበረሰብ ባህል፡ እሴት ፥ ግብረ ገብነት እንዲጠበቅ ባህልና እሴቶቹ ለትውልድ ማስተማር ይገባል ያሉት ከንቲባ አዳነች ማንነቱን ጠንቀቆ የሚያውቅ ትውልድ ደግሞ ባህሉን ይጠብቃል፤ የህዝብን ሞራል ይጠብቃል ብላዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቱባ ባህሎች እናት ናት :: በብዝሃ ማንነት፥ ባህል የተገነባች ጠንካራ ሃገር ነች ፥ የብዝሃ ማንነትና ባህሎች መገለጫ የሆነቸውን አዲስ አበባ በውስጧ የያዛቸውን ውብ ባህላዊ እሴቶቻችን ለሥራ ዕድል ፤ ለገቢ ማግኛ አድርገን አዳብረን ልንጠቀማቸው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል ::
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የብዝሃ ባህልና ፥ ቋንቋ እና ሃብቶች ባለቤት የሆነቸው ኢትዮጵያ ህዝቦች ማንነታቸውን ጠብቀው ተደጋግፈውና ተሳሰረው እንደኖሩ ያስቻሉ አኩሪ ቅርሶች ናቸዉ ብለዋል።
በሁሉም የኢትዮጰያ ጓዳዎች እጅግ ውብ የሆኑ ቱባ ` ባህሎች አሉን። ባህላዊ የእርቅ ፣ የዳኝነት ስርዓተ ፡ አቅመደካሞችን በደቦ ማገዝ ፥ የተራበን ማብላት ፥ አንዳችን በአንዳችን የመቆም ድንቅ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ናቸው፡፡
አዲስ አበባ የብዝሃ ብሔር ፡ ባህል ፦ ስነ ጥበብ : ከነጥበብ የያዘች ከተማ ናት የሉት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ የከተማዋን እድገት እየቀየሩ ያሉ የፓርኮች፥ መናፈሻዎች ፥ የመዝናኛ ቦታዎች ግንባታ ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል ::
ብርቅ እና ውብ ባህሎቻችን በመጤ ባህሎች እንዳይሽርሽሩ መንከበከብና መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳ ለ14ኛ ጊዜ በአዲስ ኣበባ እየተከበረ ያለው የባህል ፌስቲቫል በርካታ ውብ ባህሎቻችን ለህዝብ በአንድ በታ ላይ ተሰብሰባው የሚታዩበት በመሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች መጥተው ጎብኝተዋል፡፡