18 ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በድል ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ልዑክ አ/አበባ ሲደርስ በኤርፖርት አቀባበል ተደረገለት ::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ገዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተፋዬ እና ሌሎች የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎች በድል አጠናቆ የተመለሰዉን የአትሌቲክስ ልዑክ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል ::
በአሜሪካ አሪገን የተካሄው 18 ኛውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በ 4 የወርቅ፣ 4 የብር፣ 2 የነሃስ፣ በድምሩ 10 ሜዳልያዎችን በመውሰድ ከአለም አዘጋጇን ሃገር አሜሪካንን በመከተል የ2ኛ ደረጃን በመሆን ማጠናቀቁ ይታወቃል።
በድል የተመለሰው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ላሳየው ኢትዮጲያዊ ጀግንነት እና ላስገኘው ውጤት ከተማ አስተዳደሩ የምስጋና መርሃ ግብር ነገ ያካሄዳል ።