“ለኢትዮጵያ የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን” :-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳስታወቁት ድል የገቡትን ቃል በማክበር፣ለቃል ታምኖ በመሥራትና ቃልን በተግባር በመግለጥ የሚገኝ ነው ብለዋል፡፡
ቃል ማክበር ካለ የድል ብሥራት አለ፤ ለኢትዮጵያ የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን ብለዋል።
መንግሥትና ህዝብ የሚኖሩት በቃል ኪዳን ነው፤ እንደ መንግሥትና እንደ ሕዝብ ለገባናቸው ቃል ኪዳኖች ታማኞች ከሆንን ሀገር ሰላም፣ ምቹና ባለጸጋ ትሆናለችም ነው ያሉት።
ቃል ኪዳን የዓለም ህልውና የተመሠረተበት ሥርዓት ነው፤ ሰው ከሰው፣ ሰው ከአካባቢው፣ አካባቢ እርስ በርሱ ተጠባብቆና ተግባብቶ የሚኖረው በቃል ኪዳን ነው ብለዋል።