‹‹ በግንባርም በደጀንም ከፊት ሆነው በጀግንነት ለመሩት፡ ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትርና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶክተር ዐብይ አህመድ፣ ለጦር አመራሮች፤ ለመላዉ የጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን አባላትና ለፌደራልና ለክልል ፀጥታ ሀይሎች፣ ለአማራና ለአፋር ህዝብ፣ በቃ /No More/ ብላችሁ የኢትዮጵያን አንድነት አንግባችሁ ድምፃችሁን ለዓለም ያሰማችሁ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ለመላው የሀገራችን ሰላም ወዳድ ህዝቦች እንዲሁም ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብላችሁ ህይወታችሁን፣ ጉልበታችሁን፣ ሃብታችሁን፣ እውቀታችሁንና ጊዜያችሁን በመስጠት በሁሉም አውደ-ግንባሮች ሚናችሁን ለተወጣችሁ ሁሉ፡ ለሠራችሁት አኩሪ ታሪክ ከልብ የመነጨ አድናቆትና ልባዊ ምስጋናችንን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ህዝብ ስም ለማቅረብ እንወዳለን፡፡››
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ