በምክር ቤቱ የከተማው ምክር ቤት አባላት ፤ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የከተማው ከፍተኛ አመራሮችና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
የምክር ቤቱ ጉባኤ በኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር ጉባኤውን ቀመክፈቻ ንግግር በይፋ አስጀምረዋል።
ምክር ቤቱ በሁለት ቀን ቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የከተማ የአስተዳደሩን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚገመግም ሲሆን የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች የስድስት ወራት አፈጻጸም፣ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ተወያይቶ ማጽደቅ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሹመቶችን ማጽደቅም የምክር ቤቱ የሁለቱ ቀናት አጀንዳዎች ናቸው፡፡