👉 የምግብ ዘይት በህገወጥ ክምችት የተገኘውንም ጨምሮ በተለያዩ አቅራቢዎችም እንዲቀርብ በማድረግ ለጊዜው ከ2 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት እያሰራጨን እንገኛለን፡፡ ህብረተሰቡ በአካባቢው ባሉ ሸማች ሱቆች ማግኘት ይችላል!
👉 የሸገር ዳቦ የስንዴ አቅርቦት ችግር ለመፍታት በከተማ አስተዳደሩ 613 ሚሊዮን ብር ድጎማ በማድረግ፣ እንዲሁም በፋብሪካው 198 ሚሊዮን ብር በድምሩ 812 ሚሊዮን ብር በመመደብ የዳቦ ምርት ማስጀመር ችሏል፡፡
ከነገ ጀምሮም ምርቱ ወደ ገበያ የሚወጣ በመሆኑ ህብረተሰቡ የሸገር ዳቦ በምናሰራጭባቸው ማዕከላት ዳቦ ማግኘት ይችላል!