የከተማችን ነዋሪ እንደተለመደው ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት ተላልፏል፡፡
*******
ጥር 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ/ም 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል:: ከዚህ ጉባኤ ቀደም ብሎ ጥር 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ/ም 40ኛው የህብረቱ አባል ሀገራት የሚኒስትሮች ሥራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይልም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ኢትዮጵያ ማስተናገዷ የሀገራችንን እና የከተማችንን መልካም ገፅታ ከመገንባት አኳያ የራሱን አስተዋፅኦ የሚያበረክት ስለሆነ ጉባኤው ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ የሰላሙ ባለቤት የሆነው ህዝባችን እንደሁል ጊዜው ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ – ኃይል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ይሁን አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥመው ጥቆማ ለመስጠት በመደበኛ ስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11፣ 011-5-52-63-03 ፣ 011-5-52-40-77 ፣ 011-5-54-36-78 ፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም 987 ፣ 991 እና 916 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚችል ግብረ – ኃይሉ እያስታወቀ
• ከአዋሬ በጥይት ቤት ወደ ፓርላማ
• እንዲሁም ከቡልጋሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት የሚወስዱ መንገዶች በሁለቱም አቅጣጫ የስብሰባው ተካፋዮች ጠዋት ለስብሰባ ፣ ለምሳና ከሰዓት በኋላ ከስብሰባ ሲወጡ እነዚህ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት ፤ ለአጀብ ስራ መንገድ ሲዘጋ ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆን ድረስ አሽከርካሪዎች ትዕግስት ተላብሰው በመጠበቅ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያርጉ የፀጥታ ና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ጥሪውን እያቀረበ ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡-
• ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር – መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ – ኦምሎፒያ – ወሎ ሰፈር – ጃፓን ኤምባሲ -ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ -ኤርፖርት
• ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሄራዊ ቤተ – መንግስት -በፍልውሃ – በብሄራዊ ቲያትር- ሜክሲኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ ፡-
• ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት – ወዳጅነት ፓርክ – ንግድ ማተሚያ ቤት – ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር -ሜክሲኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት
• ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቲያአትር ዙሪያውን ፦
• ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ-አፍሪካ ህብረት ዋናው በር-ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከዓርብ ጥር 27 ቀን / 2014 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ሲሆን
• ከጦር ሃይሎች – ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ፦
• በኮካ-ኮላ ድልድይ – በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር- ጎማ ቁጠባ
• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ፡-ሳር ቤት-ካርል አደባባይ – በልደታ አድርገው ወደ መርካቶ እና ጎማ ቁጠባ
• የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች፦
• በአትላስ – ዘሪሁን ህንፃ- ሲግናል
• ቀለበት መንገድ – ቦሌ ሚካኤል-ሃኪም ማሞ – ወደ ጎተራ
• ቀለበት መንገድ – መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ – እንግሊዝ ኤምባሲ
• ቀለበት መንገድ -መገናኛ – አድዋ ጎዳና – አዋሬ – ቤልኤር
• በፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ መስቀል ፍላወር መጠቀም እንደሚቻል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን