የመስሪያ ሼዶቹ በ2015 በጀት ዓመት የተገነቡ ሲሆን 4ሺህ የሚሆኑ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው::
ባለፈው ሰኔ ወር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት ከ2300 በላይ ሼዶች በሕዝብ ተሳትፎ ለተለዩ ከ12ሺ በላይ ስራ አጥ የከተማችን ወጣቶች ማስተላለፋችን ይታወሳል::
የከተማ አስተዳደሩ ባለፈው አንድ ዓመት በከተማችን ያለውን የመስሪያ ቦታ ችግር ለመቅረፍ እና ለወጣቶች የመስሪያ ቦታዎችን ለማመቻቸት በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ዓመት ብቻ 2ሺህ439 ሼዶችን በማዘጋጀት ከ16 ሺህ በላይ የሚሆን ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል::
ይህም ለስራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት መስጠታችንን እና በዘርፉ ፍትሐዊነትን ለማስፈን የምንሰራቸው ስራዎች የሚያሳዩ ናቸው::