ስለ ኢትዮጵያ ፈጣሪያችንን እናመሰግናለን፤ ስለ ጀግኖቻችን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን !!
ዛሬ ጀግኖቹን የኢትዮጵያ ውድ ልጆች በክብር ተቀብለን፣ እንዳከበሩን አክብረን፣ ኢትዮጵያችንን ከፍ ስላደረጉ አመስግነን ፣ደስታችንን በጋራ ተቋድሰን እንደ ከተማ አስተዳደራችን ደማቅ አቀባበል አድርገንላቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ፀጋ ምድር፣ የድንቅና ታላቅ ህዝቦች ሃገር ናት፡፡ ጀግኖቻችንም የዚህች ታላቅ ሃገር ፍሬዎች ናቸው፡፡
የከተማ አስተዳደራችን በድል ላንቆጠቆጡን አትሌቶቻችን የተለያዩ ሽልማቶችን ያበረከተ ሲሆን
•የወርቅ ሜዳልያ ላስገኙልን አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ500 ካ/ሜ መሬት
•የብር ሜዳልያ ላስገኙልን ለእያንዳንዳቸው የ350 ካ/ሜ መሬት
•የነሃስ ሜዳልያ ላስገኙልን በተመሳሳይ ለእያንዳንዳቸው የ250 ካ/ሜ መሬት
•እንዲሁም ሁለት ሜዳልያ ላስገኘችልን ለአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ከመሬቱ በተጨማሪ የወርቅ ስጦታ
•ለአትሌቶቻችን እንደ እናትም፣ እንደ አሰልጣኝም፣ እንደ አማካሪም በመሆን ለዚህ ድንቅ ድል የመራችውና የበቃቸውን ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የወርቅ ስጦታና በከተማችን በተሰየመላት አደባባይ ለሌሎች ወጣቶች ተምሳሌት በሚሆንና ክብሯን የሚመጥን ማስታወሻ የከተማ አስተዳደሩ የሚያስገነባ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡
በሻምፒዮናው ላይ ለተሳተፈው የልዑካን ቡድንም በጥቅሉ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት በጥሬ ገንዘብ አበርክቷል።
ማህፀነ ለምለሟ ኢትዮጵያ እናታችን ገና በሁሉም መስክ ደምቃና አምራ ትወጣለች፤ ጉዟችን ሁለንተናዊ ነው፡፡
ትውልዱ የአባቶቹን ጀግንነት ፣የፈጣሪውን ታላቅነትና ምህረት ፣ የዘመኑን ጥበብና እውቀት አጣምሮ በመያዝ አገሩን ወደ ታላቅነት ማማ ያወጣል!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ