በቂርቆስ ክ/ከተማ በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ሲደረግባቸው ቆዩና ዛሬ ለምረቃ የሚበቁት ከ845 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡት 105 ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁና በአጠቃላይ 250ሺህ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ለ5983 ሰዎችም የስራ ዕድል መፍጠር የቻሉ ናቸው፡፡
ከነዚህም ውስጥ
የመኖርያ ቤት ችግርን የሚያቃልሉ 5 ዘመናዊ ህንፃዎች
931 ያረጁና የተጎሳቆሉ ቤቶችን የማደስና የጥገና ስራ
በቀን 2000 ዜጎችን የሚመግቡ 3 ምገባ ማእከላት
በ8 ቦታዎች ሞዴል ከተማ ግብርና ስራዎች
በጥቅሉ 7 የዳቦ ማምረቻና ማከፋፈያ ቦታዎች
23 የሸገር ዳቦ መሸጫዎችን ማዘመንና ማሻሻል ስራዎች
12 የመንገድ ዳርና አካፋዮችን የማስዋብ ስራዎች
9 አደባባዮችን ማስዋብ ስራዎች
4 አነስተኛ ፓርኮችን የማስዋብ ስራዎች
7 የትምህርት ቤት ማስፋፍያ ግንባታዎች
2 የጤና ጣቢያ ማስፋፍያ ግንባታ
የ10 ወረዳና 1 የክ/ከተማ ህንፃ ጥገናና ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ስራዎች
3 የፖሊስ ጣቢያ እድሳትና ማስፋፍያ ስራ
2 የመኪና ፓርኪንግ እድሳት ስራ
2 የወጣት ማእከላት እድሳት ፕሮግራም
6 የመስርያ ሼዶችን እድሳት ፕሮግራም
የቄራዎች ድርጅትን አጥርና መፀዳጃ ቤት እድሳት
1 የላይብረሪ እድሳት ፕሮግራም
እንዲሁም ለነዋሪዎችም የቤት ቁሳቁስ የማሟላት ስራዎች ይገኙበታል፡፡
ከተማችንን እንደ ስሟ ውብና አበባ እናደርጋለን!!