እጣ አወጣጡ በግልፀኝነት በታዛቢዎች የፊርማ ስነስርዓት ተካሂዶ ተጠናቋል።
👉 በሁለቱም የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮግራም (ማለትም በ20/80 እና በ40/60) 25,791 ቤቶች እጣ የወጣባቸው ሲሆን በተጨማሪም በባለሶስት መኝታ 300 መቶ ቤቶችን ቀሪ ስራ በማከናወን ለነባርና አዲሰ ተመዝጋበዎች በእጣ ተካተዋል፡፡
👉 በዚህ እጣ የ20/80 ከ96% በላይ፣ በ40/60 ከ87% በላይ የግንባታ አፈጻጸም ያላቸው ቤቶችን ለዕጣ ቀርበዋል፡፡
👉 የከተማ አስተዳደሩ ባስቀመጠው ውሳኔ መሠረት የ20/80 (ስቱዲዮ፣ ባለ 1 እና ባለ 2) ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን እንዲሁም የባለ 3 መኝታ ነባርና አዲስ ተመዝጋቢዎች (2005) ዝቅተኛውን የ84 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ እንዲሁም የ40/60 ተመዝጋቢዎች ከ40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው ለእጣ ውድድር ብቁ የሆኑ እስከ የካቲት 21/2014 ዓ.ም ድረስ(ማለትም መረጃ መውሰጃ የመጨረሻ ቀን – cut off period)፣ መሰረት መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ከባንክ በተገኘው መረጃ ላይ ተመስርቶ የመረጃ ማጥራት ኮሚቴው ባጠራውና ባደራጀው የመጨረሻ ሰነድ ተካተዋል፡፡
👉 በዚሁ መሰረት በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 93,352 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 53,540 በአጠቃላይ 146,892 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው በዚህ ዙር ዕጣ ተካትው የቤት እድለኛ ለመሆን የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
👉 የቅድሚያ ተጠቃሚነት አወሳሰን በተመለከተ
• የመንግስት ሠራተኞች 20 በመቶ፣
. ሴቶች 30 በመቶ፣
. አካል ጉዳተኞች 5 በመቶ እና አጠቃላይ ተመዝጋቢዎች 45 በመቶ በዕጣ የቤት ተጠቃሚዎች የሚለዩ ይሆናሉ