የጥምቀት በዓል ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ በመሆኑ ከሀገር ውጪ ያሉ በርካታ ቱሪስቶች የሚሳተፉበት ደማቅና ውብ በዓል ነው። በዚህም በዓል ወቅት የከተማችን ህብረተሰብ በአብሮነት፣ በፍቅርን እና በመተባበር በዓሉ በጋራ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገልጿል።
በተጨማሪም በዓሉ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ እና ከበዓሉ ዓላማ ውጪ የሚንቀሳቀሱ አካላት ሲያጋጥም ለጸጥታ አካላት መረጃ በመስጠት እና በጋራ በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ በተከናወኑ የውይይት መድረኮች ተገልጿል።
በተለይም የከተማችን ወጣቶች እንደወትሮው ሁሉ በዓሉ ሰላማዊ፣ በደመቀና ባማረ ሁኔታ እንዲከበር ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ ትውፊቱ ተጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ የማድረግ ሃላፊነትም ጭምር እእንዳለባችሁ በመገንዘብ በዓሉን ለሌላ አጀንዳ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሀይሎችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ በመድረኮቹ ተመላክተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በኩል በዓሉን ሰላማዊ ሆኖ በድምቀት እንዲከበር በሁሉም መስክ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ተገልጿል።