“አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ በመድሃኔአለም አደባባይ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በእለቱ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ስፖርት አይቋረጥምና የዘወትር ስራችን አድርገን ጤናማ ማማህበረሰብ ለመፍጠር መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ በበኩላቸው ስፖርት ጤንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ ሚና ያለው በመሆኑ ሁላችንም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ መነሳሳት አለብን ሲሉ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ሲካሄድ በሰነበተው ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ወረዳዎች እውቅና ተሰጥት የቀጣይ ከተማ አቀፍ ማስ ስፖርት አዘጋጅ የሆነው ልደታ ክ/ከተማ ከአዲስ ከተማ ዋንጫውን ተረክበዋል።