ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የ90 ቀናት ሰው ተኮር እና የሌማት ትሩፋት ፕሮጀክቶችን አስመርቀዋል::
በከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ በዘጠና ቀናት ዉስጥ ተሰረተዉ የተጠናቀቁ እነዚህ ፕሮጀክቶች የሞዴል መንደሮች፣ 28 የዶሮ ዕርባታ ሼዶች ፣ 5 የከብት እርባታ ሼዶች ፣ 5 ዳቦ መጋገሪያ ፋብሪካዎች ፣ 2 የምገባ ማዕከላት እንዲሁም ሞዴል የከተማ ግብርና ናቸው፡፡
የነዋሪዎቻችንን ችግሮች ደጋግሞ በማውራት የኑሮ ጫናን ማስቀረት አይቻልም ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከችግሮቹ እንደምናሻገረው አምኖ የመረጠንን ህዝብ ዝቅ ብለን በማገልገል ለውጥ ማምጣት እንደምንችል እነዚህ ፕሮጀክቶች ማሳያ ናቸው ብለዋል::
የሕዝቡን የኑሮ ጫና በማቅለልና የተጀመረውን ሁለንተናዊ ዕድገት በማፋጠን ረገድ የላቀ ሚና ያላቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች በ90 ቀናት ውስጥ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውንም ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል::
እነዚህን ስራዎች በመደገፍ ካገኙት ላይ ለህዝባቸው ያጋሩትን ሚድሮክ ቢዝነስ ግሩፕ እና ሣሮን አለኮ እንዲሁም ሌሎች ልበ ቀና ባለሀብቶች ላደረጉት ድጋፍ በነዋሪዎቹ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል: