አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)ሚያዚያ 5/2015 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤና የኢድ አል-ፈጥር በዓላትን ምክንያት በማድረግ 3ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ማዕድ አጋሩ።
በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ በከንቲባዋ የተደረገው ማዕድ ማጋራት በአዲስ አበባ የትንሳኤና የኢድ አል-ፈጥር በዓላትን ምክንያት በማድረግ ለ256 ሺህ ዜጎች ማዕድ ለማጋራት የተያዘው መርሀ-ግብር አካል ነው።
የማዕድ ማጋራት መርሀግብሩ በሁሉም ክ/ከተሞች እና ወረዳዎች እየተከናወነ ይገኛል፡፡