የብልጽግና ፓርቲ አመራር ውይይት መድረክ አመራሩ ከፈተናዎች በላይ ከፍ ብሎ በመገኘት ተግዳራቶችን እንዲመክት አቅም እና ዝግጁነት የፈጠረ ነዉ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ ገለፁ።
“መፍጠንና መፍጠር፣ የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል አቅጣጫ” በሚል መልዕክት በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል አመራሮች ከሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የተካሄደው የውይይት መድረክ ተጠናቋል።
በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት ፣ የውይይት መድረኩ አመራሩ እያጋጠሙ ካሉ ተግዳራቶች በላይ ከፍ ብሎ ፈተናዎችን እንዲመክት ተጨማሪ አቅምና ዝግጁነት የፈጠረ ነው።
መድረኩ በወል እውነቶች ላይ የጋራ አረዳድ ለመፍጠር፣ የመፍጠንና የመፍጠርን እሳቤዎች ፖለቲካዊ ፋይዳና እንዴትነት በመረዳት ብልጽግና ፓርቲ የተጣለበትን ታሪካዊ ሀላፊነት ለመወጣት አቅም የፈጠረ መሆኑን ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።
በቀጥታና በተዘዋዋሪ በሀገራዊ ሁኔታው ላይ አዎንታዊና ኣሉታዊ አዝማሚያ የሚያስከትሉ ዓለም ዓቀፋዊና ቀጠናዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በስኬቶችና በፈተናዎች አንድምታ ላይም ሰፊ ውይይት መካሄዱን መጠቆማቸውን።
መፍጠንና መፍጠር ፣ የወል እዉነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል አቅጣጫ” በሚል መሪ መልዕክት ሲካሄድ በቆየዉ የደቡብ ክልል አመራሮች የውይይት ማጠቃለያ መድረክ በተነሱ ጉዳዮቸ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል::