ከዛሬ 81 ዓመት በፊት ሚያዝያ 27/1933 ዓ.ም ጀግኖች አርበኞች በዱር በገደል ተዋድቀው ፋሽስት ጣልያንን በማሸነፍ የኢትዮጵያን ድል ያበሰሩበት ዕለት ነው – የአርበኞች ቀን መታሰቢያ በዓል።
በአሉ በመከላከያ ሰራዊት ማርሽ ባንድና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሃውልት እየተከበረ ነው።
በመታሰቢያ በአሉ አባትና እናት አርበኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበባት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል