አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከ36 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ መስሪያ ሼዶችን አገልግሎት ያስጀመሩ ሲሆን ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር በበኩላቸው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ከ53 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት የተገነቡ የመስሪያ ሼዶችን አገልግሎት አስጀምረዋል::
የመስሪያ ሼዶቹ የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ህዝቡ ያነሳውን ጥያቄ የሚመልሱ ከመሆናቸውም ባሻገር የዜጎችን የመስሪያ ቦታ ችግር የሚቀርፉ ፣መንግስት ለህዝቡ ቃል የገባውን በተግባር የሚያረጋግጡ ናቸው።