About ALEMSTEHAY ASHINE

This author has not yet filled in any details.
So far ALEMSTEHAY ASHINE has created 333 blog entries.

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1498ኛው የመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር ፣የደስታ ፣ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። መልካም በዓል ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

2023-09-26T20:30:53+03:00

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1498ኛው የመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር ፣የደስታ ፣ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። መልካም በዓል ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1498ኛው የመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር ፣የደስታ ፣ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። መልካም በዓል ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ2023-09-26T20:30:53+03:00

በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ።

2023-09-26T19:37:25+03:00

ከመስከረም 3 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል። በማጠቃለያ መድረኩም የፓርቲው ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የስልጠናውን ማጠቃለያ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት የስራ ስምሪት ሰጥተዋል። ስልጠናው ወሳኝ በሆኑ ሃገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የፈጠረ ሲሆን ከመላው ሃገራችን የተውጣጡ ሁለት ሺህ የፓርቲያችን አመራሮች ተሳትፈዋል። የአቅም ግንባታ ስልጠናው በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች በቀጣይነት የሚሰጥ ይሆናል።

በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ።2023-09-26T19:37:25+03:00

ዛሬ ማለዳ የመስቀል ደመራ በአልን በማስመልከት የተለያዩ የእምነት አባቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የፅዳት መርሐግብር በመስቀል አደባባይ ተከናውኗል::

2023-09-26T10:27:39+03:00

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቋንቋ ፣ ባህልና ሃይማኖት ቢኖረንም ከሌላው አለም ለየት የሚያደርገን በፍቅርና በመቻቻል በአብሮነት የምንኖር መሆናችንና አንዳችን ለሌላው ሃይማኖታዊ በአል የተሳካና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር መልካም ምኞት ከመግለፅ ባሻገር ለስኬቱ ተግባራዊ ድጋፍ የምናደርግ መሆናችን ነው ሲሉ አስታውቀዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በአላት በስኬት ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አቶ ጥራቱ በየነ ገልፀው በአላትን የፖለቲካ አላማቸው ማሳኪያ አቋራጭ አድርገው መጠቀም የሚፈልጉ አካላት እንዳይሳካላቸው የከተማው ነዋሪ ከአስተዳደሩ ጎን በመሆን የማይተካ ሚናውን እየተወጣ ስለሆነ አመስግነዋል:: በመርሐግብሩ ላይ የታደሙ የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ [...]

ዛሬ ማለዳ የመስቀል ደመራ በአልን በማስመልከት የተለያዩ የእምነት አባቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የፅዳት መርሐግብር በመስቀል አደባባይ ተከናውኗል::2023-09-26T10:27:39+03:00

በቦሌ ክፍለ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች ሊተላለፉ የነበሩ የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና ሰነዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

2023-09-19T14:01:03+03:00

ጌታሁን አስፋው ጌታሁን የተባለ እና በአማራ ክልል የህዝብ ሰላም እና ጸጥታን ለሚያውኩ ጽንፈኛ ሀይሎች የሎጀስቲክስ አቅራቢ እንደሆነ የተጠረጠረ ግለሰብ በክፍለ ከተማው ወረዳ ሁለት የሚገኝ ቤትን በመከራየት የተለያዩ ወታደራዊ ቁሰቁሶችን በማከማቸት ለጽንፈኛ ቡድኖቹ ለማቅረብ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ በጸጥታ ሀይሎች ክትትል ሊደረስበት ችሏል፡፡ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የጸጥታ ዘርፍ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ባካሄዱት ኦፕሬሽን ግለሰቡ ከተከራየው ቤት የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች፣ የመካከለኛ እና የረጅም ርቀት ወታደራዊ የመገናኛ መሳሪያዎች ፣ ልዩ ልዩ ትጥቆች እና ወታደራዊ አልባሳት፣ የተለያዩ ሰነዶች እና ጽንፈኛ ሀይሎቹ የሚጠቀሙባቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የጸጥታ አካላት ውጭ በግለሰቦች [...]

በቦሌ ክፍለ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች ሊተላለፉ የነበሩ የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና ሰነዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡2023-09-19T14:01:03+03:00

የኢትዮጵያዊያን ብርቱ እጆች በጽናት ታሪክ መስራት ቀጥለዋል።

2023-09-18T21:14:48+03:00

 ዛሬ በተጠናቀቀው የክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ካቀድነው በላይ አሳክተን 7.5 ቢሊየን ችግኞችን መትከል ችለናል። ህዝባችን ያሳየውን ትጋትና እና ብርታት መንግስት በእጅጉ ያከብራል ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር)

የኢትዮጵያዊያን ብርቱ እጆች በጽናት ታሪክ መስራት ቀጥለዋል።2023-09-18T21:14:48+03:00

በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዛሬ ትምህርት መሰጠት ጀምሯል::

2023-09-18T12:15:11+03:00

በከተማ አስተዳደሩ በዛሬው እለት የ2016 የትምህርት ዘመን የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን እንዲሁም የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ትምህርት መሰጠት ጀምሯል። በትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ቁሳቁሶች ለተማሪዎች ተሰራጭተዋል::

በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዛሬ ትምህርት መሰጠት ጀምሯል::2023-09-18T12:15:11+03:00

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀመጠ

2023-09-18T09:48:55+03:00

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል። የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አደም ፋራህ እንደተናገሩት፥ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የ2015 ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀምና ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ እንዲሁም የ2016 አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቷል። በተጨማሪም የሰላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር እና አገራዊ ሁኔታ ላይም መምከሩንም ነው የተናገሩት። በምርጫ ወቅት ፓርቲው ለህዝብ ቃል ከገባቸውን እና በመጀመሪያው የፓርቲው ታሪካዊ ጉባኤ በተቀመጡት አቅጣጫዎች አፈጻጻምን የገመገመ ሲሆን፤ ከዚህም በመነሳት የ2016 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል። በውይይትም በፓርቲው ውስጥ አባላቱ የጋራ አመለካከት እንዲይዙ ከማድረግ አንጻር ውጤት መመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን፤የአመራር ዲሲፕሊን መሻሻል ማሳየቱንና የመፈፀምና ማስፈፀም አቅም እየጎለበተ መምጣቱንም ተናግረዋል። የፓርቲውን ተቋማዊ [...]

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀመጠ2023-09-18T09:48:55+03:00

የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከል ሸማችን ከአምራች ማገናኘቱን ቀጥሎአል::

2023-09-15T15:33:03+03:00

በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዘመናዊ የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከል አምራቾች ምርቶቻቸውን በጅምላና በችርቻሮ ለሸማቾች በማቅረብ ላይ ይገኛሉ:: ማዕከሉ ከተመረቀ ጀምሮ የተሟላ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የከተማችን ነዋሪዎች ምቹ ሆኖ በተገነባው በዚህ የገበያ ማዕከል በመገኘት ያሻቸውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ከማዕከሉ እንዲሸምቱ ለማሳሰብ እንወዳለን::

የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከል ሸማችን ከአምራች ማገናኘቱን ቀጥሎአል::2023-09-15T15:33:03+03:00

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እውቅና ተሰጥቷቸዋል::

2023-09-15T01:34:21+03:00

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን አዲስ አበባ ሰላም እና አብሮነት እንዲጎለብት ፣ በተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎች አመራሩንና ህዝቡን በማስተባበር ዝቅ ብለው የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ እያደረጉት ላለው ተግባር እና ከሁሉም የሃይማኖር ተቋማት ጋር በቅርበት ፣ በእኩልነትና በፍትሃዊነት በመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት የአዲስ አበባ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ እውቅና ሰጥቷቸዋል:: በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሰጣቸው እውቅና ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እውቅና ተሰጥቷቸዋል::2023-09-15T01:34:21+03:00

የአረጋውያን መጦሪያ ፣ መጠለያና እንክብካቤ ማእከል በነገው እለት ይመረቃል፡፡

2023-09-14T11:46:43+03:00

ለ730 አረጋውያን እንክብካቤ የማድረግ አቅም ያለው ይህ የመጠለያ እና መጦሪያ ማዕከል በነገው ዕለት ይመረቃል:: ማዕከሉ በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን ለአረጋዊያን የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮች እና ፋርማሲ ፣ የምግብ ማብሰያና የመመገቢያ አዳራሽ ፣ የመኝታ ቤት ፣ ላውንደሪና የአረጋዊያን ንፅህና መጠበቂያ ፣ የእደ ጥበብ መስሪያ እና የመዝናኛ ቦታዎችን ያከተተ ነው፡፡ ማዕከሉ ተገንብቶ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ የከተማ አስተዳደሩ ሰፋ ያለ መሬት አቅርቦ የሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን እንዲገነባ በተደረገው ስምምነት መሰረት ግንባታውን በጥራት በማጠናቀቅ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ስለተወጣ በተገልጋይ አረጋዊያን ስም ልናመሰግን እንወዳለን::

የአረጋውያን መጦሪያ ፣ መጠለያና እንክብካቤ ማእከል በነገው እለት ይመረቃል፡፡2023-09-14T11:46:43+03:00
Go to Top